img

ልጅሽ የምትጠቀመው ፖፖ ሙሉ በሙሉ ልብሷን የማያስወልቃት ወይም የማይቆረቁራት ..

ፖፖ ወይም ሽንት ቤት ለመጠቀም የሚያስቸግሩ ልጆችን ምን መፍትሄ አለ ? 
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
1- ልጅሽ የምትጠቀመው ፖፖ ሙሉ በሙሉ ልብሷን የማያስወልቃት ወይም የማይቆረቁራት ወይም ተቀምጣ ስትነሳ እግሯን የማያሳምማት መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርብሻል ።

2- ልጆች በተለይ ባንቺ ልጅ እድሜ አካባቢ ያሉ ልጆች ጨዋታ ማቋረጥ በፍፁም አይፈልጉም ስለዚህ ጨዋታቸው ሳይቋረጥ መሽናት ስለሚፈልጉ ባገኙት ቦታ መሽናት ይመርጣሉ። ስለዚህ ፖፖውን ጨዋታ የምታዘወትርበት አካባቢ ሁልግዜም አድርጊው ።

3- ቀስ በቀስ ለማለማመድ ሞክሪ እንጂ በፍፁም በአንዴ ለማስለመድ አትሞክሪ። ይህ ልጅሽ ግትር እንድትሆን ያደርጋታል ።

3- ሽንት ወለል ላይ ይታየኛል ወይም ልብስሽ በሽንት ርሷል በማለት የሚታይሽን ግለጪ እንጂ ፍርድ አትስጪ።  ለምን ሸናሽ? ወይም ልክ አይደለሽም መንፈስ አታሳያት። ልክ ያልሆነን ነገር ስታሳውቂያት በራሷ ስህተቱን እንድትረዳና ስህተቷን በራሷ እንድታርም ያግዛታል ።

4- ፖፖላይ ስትሸና ደግሞ እውቅና ስጫት። ኦው ፖፖ ላይ ሸናሽ? ጎበዝ! በያት። አንዳንድ ግዜ መሸለምም አይከፋም ፣ በሸናች ቁጥር መጫወቻ ግዢላት ሳይሆን በጣም የምትወደውን ነገር አድርጊላት ለማለት ነው ።

5- ልጆች ትኩረት ሲፈልጉ አዋቂዎች ልንረዳበት ከምንችለው ውጪ በሆነ ባህሪ ሊያሳዩ ይችላሉ። ያላግባብ  ስትሸና  ትኩረት መንፈግ መፍትሄ ሊያመጣ ይችላል። መምታት መቆጣት ወይም በሌላ መልኩ መቅጣት ነገሩን ያባብሰዋል እንጂ አያሻሽለውም ።

5- ፖፖ ማስለመድ ላንቺም ለልጅሽም የሚያስጨንቅ ጉዳይ ሊሆን አይገባም። በዚህ ጉዳይ ብዙ ወላጅ ጭንቀት ውስጥ ይገባል አንዳንዱ ራሱን ጥሩ ወላጅ አይደለሁም በሚል ሌሎች ወላጆች ደግሞ ልጆቻቸውን በመውስ ይረበሻሉ። ጭንቀትሽን ቀንሽ ዘና ብለሽ ልጅሽም ዘና እንድትል አድርጊያት። ባላሰብሽው ወቅት ልጅሽ ፖፖ ላይ ባግባቡ ስትጠቀም ታገኛታለሽ ። 
ባግባቡ ሽንት ቤት መጠቀም እስከ አራት አመት ሊፈጅ የሚችል ጉዳይ ስለሆነ አትጨነቂ።

ላለዎት ጥያቄ በቂ ማብራሪያ ለማግኘት የዩሮሎጂ ስፔሻሊስታችንን ዶር መዝገብን ኢትዮ ስካንዲክ ስፔሻሊቲ በመምጣት ወይም 0944724444 ላይ በመደወል ቀጠሮ ይያዙ። መምጣት ካልቻሉ 0911 149869 ላይ በመደወል ነፃ የማማከር አገልግሎት ወይም ቴሌግራም ግሩፓችንን በመቀላቀል የተለያዩ የጤና ምክሮችን ያግኙ https://t.me/ethioscandic.