img

የፕሮስቴት እጢ ከወንዶች ጋር አብሮ የሚፈጠር ከዘር መራቢያ አካላት አንዱ ሲሆን እድሜያቸው ከ45 በላይ ሲሆን መፋፋት ወይም ማደግ ይጀምራል

የፕሮስቴት እጢ ከወንዶች ጋር አብሮ የሚፈጠር ከዘር መራቢያ አካላት አንዱ ሲሆን እድሜያቸው ከ45 በላይ ሲሆን መፋፋት ወይም ማደግ ይጀምራል ፡ ይህንንም የፕሮስቴት እጢ መፋፉት (BPH) በማለት እንጠራዋለን ፡ የፕሮስቴት እጢ የሚገኘው የሽንት ፊኛ በር ላይ ስለሆነ ማደግ ሲጀምር የተለያዩ የሽንት ችግሮች ያመጣል ፡ የፕሮስቴት እጢ መፋፉት ሽንት ላይ ችግር እስካልፈጠረ ድረስ እንደ ተፈጥሮ ሂደት እንጂ እንደ በሽታ አይታይም በመቆየትም ወደ ካንሰር አይቀየርም ፡ የፕሮስቴት እጢ መፋፉት በራሱ በሽታ ስላልሆነ ምንም አይነት ህክምና አይፈልግም ሽንት ላይ ምልክቶች ሲያሳይ ግን ህክምና ይፈልጋል ፡ ሽንት ላይ ከሚያሳያቸው ምልክቶች ውስጥ የሽንት መቆራረጥ ፣ ሲወጣ ማስቸገር ፣ በጣም ቀጭን ሆኖ መውረድ ወይም እስከነጭራሹ ሽንት መከልከል ።  
ሌሎች ምልክቶች የሽንት ማጣደፍ ፣ አልፎ አልፎም አጣድፎ ማምለጥ ፣ ለሊት ላይ ለሽንት መመላለስ ሊሆን ይችላል ፡ እነዚህ ምልክቶች ካሉ ሀኪም ማየት ያስፈልጋል ፡ ፕሮስቴት ካንሰር ራሱን ችሎ የሚመጣ በሽታ ሲሆን ምልክቶቹ ከላይ የተጠቀሱት ጋር ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል ፡ በመሆኑም የፕሮስቴት እጢ መፋፉት ጋር ለመለየት የተለያዩ ምርመራዎች ይደረጋሉ ፡ ላለዎት ማንኛውም ጥያቄ ከስፔሻሊስት ሃኪሞቻችን ማብራሪያ እንዲያገኙ በስልክ ቁጥር 0944-72-44-44 መልክትዎን ያስቀምጡ ወይንም በቴሌግራም ግሩፕ እና ፌስቡክ ሜሴጅ ይላኩልን ፡ ደውለን ነጻ የማማከር አገልግሎት እንሰጥዎታለን ፡፡