img

የተወሰኑ ሰዎች በመኪና፣ በባቡር፣ በአውሮፕላን ወይም በጀልባ/መርከብ ሲጓዙ ማዞርና ማስመለስ ይገጥማቸዋል። ይህ የሚከሰተው በጆሮአቸው ውስጥ ያሉ ሚዛን ጠባቂ አካላት የሚያነቡት ...

የተወሰኑ ሰዎች በመኪና፣ በባቡር፣ በአውሮፕላን ወይም በጀልባ/መርከብ ሲጓዙ ማዞርና ማስመለስ ይገጥማቸዋል። ይህ የሚከሰተው በጆሮአቸው ውስጥ ያሉ ሚዛን ጠባቂ አካላት የሚያነቡት፣ አይናችን የሚመለከተው እና የሰውነታችን እንቅስቃሴ አልባ መሆን ለአይምሮአችን የሚያስተላልፉት መልእክት ፍፁም የተለያየ ስለሚሆን በሚከሰተው የመልእክት መዘበራረቅ ምክንያት ነው። ይህ በተለይ የሚከሰትባቸው

1- በእድሜ ወጣቶች ላይ ከ50አመት በላይና ከ2አመት በታች ብዙግዜ አይከሰትም

2- ሴቶች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው

3- እርግዝናና የወር አባ ላይ የበለጠ ያጋልጣል።

4- ሚግሬይን፣ ጭንቀት እና የጆሮ ውስጥ ህመም የበለጠ ተጋላጭ ያደርጋሉ

5- በቂ እንቅልፍ አለመተኛት

6- ከጉዞ በፊት ብዙ መመገብ፣ ቅባት እና ቅመም የበዛባቸው ምግቦችን መመገብ

7- አልኮል፣ ሲጋራ ወይም ሌላ እፅ አለመጠቀም

8- ሲቀመጡ ከመኪናው ኋላ አለመቀመጥ። ፊት ወንበር ላይ መቀመጥ

9- ወደውጭ ሲያዩ ሩቅ አድማስ አካባቢ ማየት

10- ጭንቅላትዎን ቀጥ አድርገው በወንበሩ ጀርባ ላይ መደገፍ

11- ከጉዞው በፊት በሀቂ ፈሳሽ መጠጣት ቀለል ያለ ምግብ መመገብ

12 - ዝንጅብል ፣ ሎሚ ብዙዎች የማቅለሽለሽ ስሜት ስለሚያጠፋ መጠቀምን ይመክራሉ። ቢያንስ አይጎዱዎትም።

13- መከላከያ መድሃኒቶች የአለርጂ እንክብሎች ሲሆኑ እንቅልፍ እንቅልፍ የሚያስብሉት አይነቶች ይመረጣሉ።