img

የወንድ ልጅ ግርዛት በሃይማኖታዊ ምከንያት የተጀመረ ሲሆን በአሁኑ ዘመን ለጤና ባለው ጠቀሜታ እየተከናወነ ይገኛል።

የወንድ ልጅ ግርዛት በሃይማኖታዊ ምከንያት የተጀመረ ሲሆን በአሁኑ ዘመን ለጤና ባለው ጠቀሜታ እየተከናወነ ይገኛል።


ያለመገረዝ ከሚከተሉት የጤና ችግሮች ጋር ሊያያዝ ይችላል።
- ተደጋጋሚ የሆነ የሽንት መስመር ኢንፌክሽን
- የብልት መቆጣት
- የሸለፈት ጥበት/ የሸለፈት ወደሗላ የመመለስ ማስቸገርን ሊያስከትል ይችላል ።
በወጣትነት ወይም በአዋቂ እድሜ አለመገረዝ ደግሞ ለአባላዘር በሽታዎች ለኤች.አይ.ቪ የማጋለጥ እድል ሊጨምር ይችላል ፡ ብዙውን ጊዜ ባይሆንም ለብልት ካንሰርም ተጋላጭነትን ይጨምራል ።
በማንኛውም እድሜ ግርዛትን ማከናወን ይቻላል ነገር ግን ከ1 አመት በታች በተለይም ከ3 ወር በታች ቢሆን ይመረጣል ምክንያቱም ለመስራት ቀላል ነው ፣ ቁስሉ በቀላሉ ይደርቃል ፣ ከሰርጀሪ ወይም ከማደንዘዣ ጋር የተያያዘ የጎንዮሽ ጉዳት አነስተኛ ነው ፡ በጨቅላነት እድሜ የተከናወነ ግርዛት የተሻለ እይታ (Cosmetic appearance) ያለው ብልት እንዲኖር ያደርጋል።
- አብዛኛው ለሀይማኖት ተብሎ የሚደረግ ግርዛት በ7ኛው ቀን ይከናወናል ይህም ከህክምና አንፃርም ይመከራል።