img

ይህ በሴቶች እንቁላል ማኮረቻ እጢ ወይም እንቁልጢ ላይ የሚከሰት ውሃ የቋጠረ እጢ ነው። እጅግ ብዙ ሴቶች ላይ የሚከሰት ሁኔታ ነው።

ይህ በሴቶች እንቁላል ማኮረቻ እጢ ወይም እንቁልጢ ላይ የሚከሰት ውሃ የቋጠረ እጢ ነው። እጅግ ብዙ ሴቶች ላይ የሚከሰት ሁኔታ ነው። በአብዛኛው ምንም አይነት ችግር አይፈጥርም። በጣም አልፎ አልፎ በተለይም ያረጡ እናቶች ላይ ከተከሰተ የካንሰር ባህሪ ሊኖረው ስለሚችል በቂ ምርመራ ይፈልጋል። 


- ምልክቱ በሆድ የታችኛው ክፍል ላይ በቀኝ ወይም በግራ በኩል ህመም ሊኖር ይችላል
- በአልትራሳውንድ መኖር አለመኖሩ እና ባህርዩን ማረጋገጥ ይቻላል። 
- የካንሰር ስጋት ካለ የካንሰር ጠቋሚ ደም ምርመራ ማድረግ ይመከራል።
- ባብዛኛው ምንም አይነት ህክምና አይፈልግም። 


ህመሙን ለማስታገስ ቤት ውስጥ ምን ማድረግ እንችላለን?
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
- ማስታገሻ መውሰድ
- ሙቀት በታችኛው የሆድ ክፍል ላይ መጠቀም ሙቅ ውሃ የያዘ ፕላስቲክ ወይም በሙቀት የራሰ ፎጣ መጠቀም እንችላለን
- ማሳጅ ማድረግ 
- ስፖርት መስራት
- ለውዝ በብዛት መጠቀም 
- የከሞሜላ እና የዝንጅብል ሻይ ደጋግሞ መጠጣት ይረዳሉ ተብሎ ይታመናል። 


መቼ ነው ቀዶህክምና የሚፈልገው? 
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯­¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
- መጠኑ ትልቅ ከሆነ ብዙ ስፔሻሊስቶች ከ5ሴሜ ከበለጠ እንዲወጣ ይመክራሉ 
- ህመሙ በተለመዱት የማስታገሻ አይነቶች የማይመለስ ከሆነ
- መጠኑ በሂደት እየጨመረ የሚሄድ ከሆነ 
- አልትራትራ ሳውንድ ላይ ለካንሰር አጠራጣሪ ባህሪ ካለው 
- በእድሜ የገፉ እናቶች ላይ ከተከሰተ 
- ከፈረጠ ወይም ኦቫሪው እንዲጠማዘዝ ካደረገ

 

መቼ  አስቸኳይ ህክምና ቦታ መሄድ አለብኝ? 
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
- ድንገተኛ እና ከፍተኛ ህመም ካመጣ 
- ህመሙ ከትኩሳት ጋር አብሮ ከመጣ
- ህመሙ ከተደጋጋሚ ማስመለስ ጋር ከተያያዘ
- ድካም፣ ማዞር አይነት ስሜቶች ካሉ 
በአስቸኳይ ሃኪም ጋር መቅረብ ያስፈልጋል።

ኢትዮ ስካንዲክ የጤና ማአከል ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሆኑ የቀድሞ የወንድይራድ ተማሪዎች እና የኮተቤ ልጆች የተቋቋመ ተቋም ሲሆን አላማው ለአካባቢው ደረጃውን የጠበቀ የህክምና አገልግሎት መስጠት እና ልዩ ልዩ በጎ አስተዋጽዎችን በማበርከት ማህበረሰቡን ማገልገል ነው ። አድራሻችን - ኮተቤ ወረዳ 13 ወሰን ግሮሰሪ አካባቢ ያገኙናል ፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0944-72-44-44 ወይም 0930-03-13-17 ይደውሉ ።