የሽንት መቅላት በብዙ ምክንያቶች ሊገለፅ ይችላል ፡ የሽንት መድማት ችግር በአይን የሚታይ (Gross Hematuria) ወይም በሽንት ምርመራ ብቻ የሚታወቅ (Microscopic Hematuria) ሊሆን ይችላል ።
- General Knowledge
- 0 Comments
የሽንት መቅላት ወይም መድማት ችግሮች (Hematuria)
የሽንት መቅላት በብዙ ምክንያቶች ሊገለፅ ይችላል ፡ የሽንት መድማት ችግር በአይን የሚታይ (Gross Hematuria) ወይም በሽንት ምርመራ ብቻ የሚታወቅ (Microscopic Hematuria) ሊሆን ይችላል ።
የተለመደ የሽንት መቅላት ወይም መድማት መንስኤዎቹ የሚከተሉት ናቸው ፡-
1. ሽንት የሚያቀሉ ምግቦች ለምሳሌ (ቀይ-ስር) ወይም መድሀኒቶች
2. ከፍተኛ የሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለምሳሌ (ረጅም ርቀት ሩጫ)
3. የኩላሊት ወይንም የሽንት ፊኛ ኢንፌክሽን
4. የኩላሊት ወይንም የሽንት ፊኛ ጠጠር
5. የፕሮስቴት እጢ መፋፋት
6. የፕሮስቴት እጢ ካንሰር
7. የኩላሊት ብግነት ወይም መቆጣት (Glomerulonephritis)
8. የሽንት ፊኛ ወይም የኩላሊት ካንሰር
9. በአደጋ ምክንያት የተከሰተ የኩላሊት ፣ የፊኛ ወይም የሽንት ቱቦ ጉዳት
የሽንት መድማት ችግር ከቀላል እስከ ካንሰር የመሳሰሉት ከባድ ችግሮች ምልክት ስለሆነ ችግሩ ከተከሰተ ሀኪም ጋር ቢቻል ዮሮሎጂስት ጋር ቀርቦ መሰረታዊ ምርመራዎችን ማድረግ ያስፈልጋል ።
ለማንኛውም የኩላሊት ፣ የሽንት ፊኛ ወይም የፕሮስቴት ችግሮች እንዲሁም የወንድ ተዋልዶ ችግሮች በስልክ ቁጥር 0911-14-98-69 የኢትዮስካንዲክ ክሊኒክ ዮሮሎጂስቶችን ማማከር ይችላሉ ፡ በተጨማሪም በክሊኒካችን ዘወትር ሰኞ እና ሀሙስ ከ8፡00 ሰአት ጀምሮ በአካል ኮተቤ ወረዳ 13 ወሰን ግሮሰሪ አካባቢ በሚገኘው ክሊኒካችን በአካል ዶክተሮቹን ማግኘት ይችላሉ ።
0 Comments